ስለ እንስሳት እንክብካቤና ጥበቃ ምን ያህል ያውቃሉ? ምን ያህልስ ለእንስሳት ጥበቃና ከለላ ያደርጋሉ?

መጋቢት 1-11/2017 ዓ.ም


እንስሳት ፍቅር እንክብካቤና ክብር የሚገባቸው ስሜት ያላቸው ፍጡራን ናቸው። በሀገራችን የማህበረሰቡ ኑሮ በእጅጉ ከእንስሳት ጋር የተቆራኘ በመሆኑ እንስሳት ለሰው ልጆች ያላቸውን ፋይዳ ማንም የሚዘነጋው አይደለም።
ይሁን እንጂ የሚሰጡትን አገልግሎትና ጥቅም በዘነጋ መልኩ በሰው ልጆች እንስሳት በርካታ በደሎች ይፈጸምባቸዋል። ፍቅር ይነፈጋሉ፤ ቀላል የማይባል የጭካኔ ተግባር ይፈጸማቸዋል፤ ይደበደባሉ፤ ፤ ከአቅም በላይ ስራ እንዲሰሩ ይደረጋልም፤ ሲከፋም ይገደላሉ።
በዚህም በሽዎች የሚቆጠሩ እንስሳት ህይወታቸው ያለእድሜያቸው ይቀጠፋል። በተለይ ተገቢውን አገልግሎት እየሰጡ እንኳን በቸልተኝነት በቂ ምግብ፣ ውሃ፣ መጠለያ እና አስፈላጊ ህክምና በወቅቱ እንዲያገኙ አይደረግም።
በአካባቢያችንም እንስሳት ይደበደባሉ፤ ከአቅም በላይ ስራ እንዲሰሩ ይደረጋሉ፤ ለእንስሳት ከለላና ጥበቃ የወጡ ህጎች አይተገበሩም። ህብረተሰቡም በደላቸውን በአደባባይ እያየ ከሚደርስባቸው ስቃይ እና ጉዳት አይታደጋቸውም።
ስለዚህ እንስሳት ያላቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ሳትዘነጉ የእንስሳትን ሰብአዊ የአያያዝ ልምዶችን በመተግበር የሚሰሩ እንስሳትን

  • ደህንነት ያረጋግጡ!
  • ከስራ በኋላ በቂ እረፍት፣ ተገቢና ወቅታዊ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ያድርጉ!
  • ከመጠን በላይ ከማሰራትና ከመጫን ይቆጠቡ!
  • በእንስሳት ላይ የሚደርሱ ማናቸውንም ጭካኔ የተሞላባቸውን ድርጊቶች ያጋልጡ!
  • ትኩረት የሚሹ እንስሳትን ይንከባከቡ!
  • መቼም የትም በምንም ሁኔታ ድምፃቸው ይሁኑ!
  • በእንስሳት ላይ የሚፈጸሙ በደሎችን ካዩ አይለፉ!
  • ለሚመለከተውም አካል ሪፖርት ያድርጉ!


በማለት መልዕክታችንን እናስተላልፋለን::
የኢትዮጵያ የእንስሳት ሀኪሞች ማህበር ከዓለም የእንስሳት ደህንነት ጥበቃ ስፓና (GLOBAL SPANA) ጋር በመተባበር


This message was produced for the Afar region (Gewane district, Semera and its surrounding) and the Amhara region (Dessie, Kombolch and Harbu towns).

Summary
ስለ እንስሳት እንክብካቤና ጥበቃ ምን ያህል ያውቃሉ? ምን ያህልስ ለእንስሳት ጥበቃና ከለላ ያደርጋሉ?
Article Name
ስለ እንስሳት እንክብካቤና ጥበቃ ምን ያህል ያውቃሉ? ምን ያህልስ ለእንስሳት ጥበቃና ከለላ ያደርጋሉ?
Description
እንስሳት ፍቅር እንክብካቤና ክብር የሚገባቸው ስሜት ያላቸው ፍጡራን ናቸው። በሀገራችን የማህበረሰቡ ኑሮ በእጅጉ ከእንስሳት ጋር የተቆራኘ በመሆኑ እንስሳት ለሰው ልጆች ያላቸውን ፋይዳ ማንም የሚዘነጋው አይደለም። ይሁን እንጂ የሚሰጡትን አገልግሎትና ጥቅም በዘነጋ መልኩ በሰው ልጆች እንስሳት በርካታ በደሎች ይፈጸምባቸዋል። ፍቅር ይነፈጋሉ፤ ቀላል የማይባል የጭካኔ ተግባር ይፈጸማቸዋል፤ ይደበደባሉ፤ ፤ ከአቅም በላይ ስራ እንዲሰሩ ይደረጋልም፤ ሲከፋም ይገደላሉ።
Publisher Name
EVA
Scroll to Top