Condolence Message: Passing of Dr. Bulto Giro

የዶ/ር ቡልቶ ጊሮ ቦሩ
አጭር የህይወት ታሪክ
ዶ/ር ቡልቶ ጊሮ ከአባታቸው ከአቶ ጊሮ ቦሩ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ነዲ ገብሳ የካቲት 12 ቀን 1944 ዓ.ም በምዕራብ
ሸዋዞን ግንደበረት ካቺስ በምትባል ቦታ ተወለዱ
እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ፤
የ1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ግንደበረት 1ኛ ደረጃ ተምረዋል፣
የ2ኛ ደረጃ ማዕረግ ህይወት ዘቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ት/ቤት እስከ 10ኛ ክፍል ተምረዋል፡፡
የዲፕሎማ ትምህርታቸውን በቢሾፍቱ እንስሳት ሕክምና ፋኩልቲ 1976 — 1978 ዓ.ም አጠናቀዋል፡፡
የመጀመሪያ ዲግሪ እና 2ኛ ዲግሪያቸውን እ.ኤ.አ 1987 — 1995 በኩባ ሀቫና ተምረዋል፡፡
የ3ኛ ዲግሪያቸውን (PhD) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንስሳት ህክምና እና ግብርና ኮሌጅ 2015 እ.ኤ.አ አግኝተዋል፡፡
ዶ/ር ቡልቶ ጊሮ በተለያዩ ሚኒስተር መ/ቤቶች ማለትም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ በግብርና ሚስቴር እና በአዲስ አበባ
የኒቨርሰቲ እንስሳት ህክምና ግብርና ኮሌጅ በማስተማር በምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎት እስከ እለተ ሞታቸው
ድረስ ሀገራቸውን በቅንነትና በታኝነት ያገለገሉ ሙህር ነበሩ፡፡
ዶ/ር ቡልቶ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና ፋኩልቲ ከተቌቌመ በኌላ ትልቅ የባለሙያ አስተዋፅኦ ካበረከቱ በቁጥር ጥቂት
ከነበሩ ሰራተኞች መካከል የሚጠቀሱ አንጋፋና ተወዳጅ ባለሙያ ነበሩ።
ዶ/ር ቡልቶ ባለትዳር እና የ3 ልጆች አባት ነበሩ፡፡
ቀብራቸው የሚፈፀማ ማክሰኞች ህዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም ጧት 5፡00 ሰዓት የቀብር ቦታ ቢሾፍቱ አቦ በክርስቲያን

 

የኢትዮጵያ እንስሳት ሐኪሞች ማሕበር ለቤተሰቦቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ይመኛል፡፡

Scroll to Top